ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በሞስኮ እንደተወያዩ ሮሳቶም አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በሞስኮ እንደተወያዩ ሮሳቶም አስታወቀ
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በሞስኮ እንደተወያዩ ሮሳቶም አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.12.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ በኢትዮጵያ መገንባት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ በሞስኮ እንደተወያዩ ሮሳቶም አስታወቀ

"ታህሳስ 9 ቀን በሞስኮ በሮሳቶም የዓለም አቀፍ ሥራዎች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ እና በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳንዶካን ደበበ በተመራ ልዑክ መካከል ውይይት ተካሂዷል...ሁለቱ አካላት በሩሲያ ዲዛይን ከፍተኛ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት ዙሪያ የተለያዩ ጉዳዮችን ተወያይተዋል" ሲል የሩሲያው ኮርፖሬሽን በመግለጫው አመልክቷል።

ከውይይቱ በኋላ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በትቬር ክልል የሚገኘውን የካሊኒን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ይጎበኛል።

በመስከረም ወር ሮሳቶም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጪያ ፕሮጀክት ለማልማት በሞስኮ የድርጊት መርኃ-ግብር ተፈራርመዋል። በዚህ ሰነድ መሠረት የፕሮጀክቱ ፍኖተ ካርታ ከተዘጋጀ በኋላ የአዋጭነት ጥናት እና በመንግሥታት ደረጃ የስምምነት ፊርማ ይከተላል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0