አሜሪካ በቬኔዙዌላ ጉዳይ 'የዓለም ፖሊስ' መሆን አትችልም - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ በቬኔዙዌላ ጉዳይ 'የዓለም ፖሊስ' መሆን አትችልም - ባለሙያ
አሜሪካ በቬኔዙዌላ ጉዳይ 'የዓለም ፖሊስ' መሆን አትችልም - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.12.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ በቬኔዙዌላ ጉዳይ 'የዓለም ፖሊስ'  መሆን አትችልም - ባለሙያ

ዋሽንግተን በሶስተኛ ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ወደ ጎን በማለት ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ "ሰበብ" እየፈለገች ነው ሲሉ አርጀንቲናዊው ዓለም አቀፍ ተንታኝ ክሪስቲያን ሪዮም ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"መጀመሪያ ሰበቡ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ነበር፤ አሁን ደግሞ ነዳጅ ሆኗል። ሰበቡ ምንም ሊሆን ይችላል፤ ትንኮሳዎቹ ግን ተበራክተዋል" ብለዋል።

አሜሪካ ሙሉ በሙሉ የቬኔዙዌላ ኃላፊነት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ የመግባት መብት የላትም፤ እንደ ባለሙያው ማብራሪያ።

ተንታኙ በተጨማሪም በቅርቡ የቀረበው አዲሱ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ፤ ላቲን አሜሪካን በዋሽንግተን ቀጥተኛ ተጽዕኖ ሥር የሚያስቀምጠውን የሞንሮ ዶክትሪን ዳግም ለማስጀመር እንደሚሻ ገልፀዋል።

"ቀስ በቀስ፤ ላቲን አሜሪካን እንደ ጓሮ፣ የአሜሪካን ጥቅም ማስጠበቂያ ክልል አድርጎ የመመልከት ሀሳብ እያየለ መጥቷል [...] እና የቬኔዙዌላ ሁኔታ እንደሚያመለክተው ይህ የሚሆነው በድርድር፣ ኢንቨስትመንት ወይም ድርድር ሳይሆን በጫና፣ ማዕቀብ እና በኃይል እንደሆነ ነው" ሲሉ ሪዮም ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0