የብሪታንያ ቅጥረኛ ከዩክሬን ጦር ኃይሎች ጋር በዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሲዋጋ ተይዞ የ13 ዓመታት እስር ተፈረደበት
19:33 18.12.2025 (የተሻሻለ: 19:34 18.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የብሪታንያ ቅጥረኛ ከዩክሬን ጦር ኃይሎች ጋር በዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሲዋጋ ተይዞ የ13 ዓመታት እስር ተፈረደበት
ሃይደን ዊሊያም ዴቪስ፤ በ2024 ክረምት ወቅት በሩሲያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ሲውል የአሜሪካ የጦር ጠመንጃ እና ጥይት ይዞ ነበር። መስከረም 2025፤ የቅጥረኛው የእስር ግዜ መራዘሙን የሩሲያ አቃቤ ሕግ ቢሮ አስታውቋል።
ዴቪስ ከዩክሬን ዓለም አቀፍ የመከላከያ ጦር ሠራዊት ጋር የጋራ ስምምነት በመፈረም ወታደራዊ ሥልጠና ወስዶ ልዩ ክህሎቶችን እና መሳሪያዎችን አግኝቷል።
የዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው፤ ፍርድ ቤት ዴቪስ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት የወንጀለኛ መቅጫ እስር ቤት በእስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የኪዬቭ አገዛዝ የውጭ ቅጥረኞችን "ለመድፍ ማረፊያነት" እየተጠቀመባቸው እንደሆነና እና የሩሲያ ጦር እነዚህን ወታደሮች መደምሰሳቸውን እንደሚቀጥሉ በተደጋጋሚ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X