የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ፀጥታን መሠረት ያደረገ የአስቻይነት የምርጫ ቀጣና ምደባ ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ፀጥታን መሠረት ያደረገ የአስቻይነት የምርጫ ቀጣና ምደባ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ፀጥታን መሠረት ያደረገ የአስቻይነት የምርጫ ቀጣና ምደባ ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ፀጥታን መሠረት ያደረገ የአስቻይነት የምርጫ ቀጣና ምደባ ይፋ አደረገ

ቦርዱ የዘንድሮው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄዱባቸው የሚችሉ አካባቢዎችን ለመወሰን ባለ ሶስት ደረጃ የፀጥታ ምደባ ስርዓት ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚህም መሠረት፦

🟢 አረንጓዴ፦ ምርጫ ማድረግ የሚቻልባቸው ቦታዎች፣

🟡 ቢጫ፦ ከጥንቃቄ ጋር ምርጫ የሚቻልባቸው ቦታዎች፣

ቀይ፦ በፀጥታ ምክንያት ምርጫ ማድረግ የማይቻልባቸው ቦታዎች ሆነው ተመድበዋል።

ከ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በመነሳት በመላ ሀገሪቱ ምርጫዎችን የማካሄድ ተፈጻሚነትን ለመገምገም ከክልል መንግሥታትና ከከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፀጥታ ተቋማት መረጃዎችን ሲሰበስብ መቆየቱ ተጠቁሟል።

ምርጫ ቦርድ በተሰበሰበው መረጃ መሠረት፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ከክልል መንግሥታትና ከከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፀጥታ ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ገልጿል።

በመጨረሻም ተጨባጭ ግምገማን ተገን አድርጎ ምርጫ ማድረግ የሚቻልባቸውንና የተለዩ አካባቢዎችን ይፋ እንደሚያደርግ ቦርዱ አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0