የአንጎላ መንግሥት ኮንጎ በደቡብ ምስራቅ ወታደሮችን ለማሠማራት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተዘገበ
18:16 18.12.2025 (የተሻሻለ: 18:24 18.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአንጎላ መንግሥት ኮንጎ በደቡብ ምስራቅ ወታደሮችን ለማሠማራት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተዘገበ
አንጎላ የኮንጎን ታላቁ የካታንጋ ክልል ለማስጠበቅ ወታደሮችን አትልክም ሲል አንድ የአንጎላ የዜና አውታር ዘግቧል።
የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አቻቸው ፌሊክስ ሺሰኬዲ፤ በኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ያለውን ቀውስ መንስኤ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንዲጀምሩ እንጂ ወታደሮችን እንዳያሰማሩ መክረዋል።
ሺሰኬዲ በሳምንቱ መጨረሻ አንጎላን በመጎብኘት ከሎሬንሶ ጋር የተገናኙ ሲሆን በትላቁ ካታንጋ ውስጥ የሚገኙትን የላይኛው ካታንጋ እና ሉአላባ የድንበር ግዛቶች ለማስጠበቅ እርዳታ ጠይቀዋል።
የኮንጎ መንግሥት የኤም23 አማፂያን በከፊል ከተቆጣጠሩት የደቡብ ኪቩ ግዛት ወደ ካታንጋ በደቡብ በኩል ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለው ተዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X