ሩሲያ የአፍሪካን የተባበረ ድምጽ እና የባለብዙ ዋልታ ዓለም ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ትደግፋለች - ላቭሮቭ

ሩሲያ የአፍሪካን የተባበረ ድምጽ እና የባለብዙ ዋልታ ዓለም ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ትደግፋለች - ላቭሮቭ
ሩሲያ የአፍሪካ አኅጉርን እንደ አጋር ብቻ ሳይሆን እንደ ሉዓላዊ ኃይል ትመለከታች ሲሉ የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር መድረክ ሁለተኛ የሚኒስትሮች ጉባኤን አስመልክቶ በአፍሪካ የሕትመት ሚዲያ ባሳተሙት ጽሑፍ ላይ ገልፀዋል፡፡
ይህ የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን የልማት ሞዴሎች እና ዓለም አቀፍ አጋሮች የመምረጥ መብት ማክበርን ያካትታል።
ከብዙ የምዕራባውያን ኃያላን በተለየ የሩሲያ ተሳትፎ የተመሠረተው በጋራ የመከባበር ታሪክ ላይ ነው። ላቭሮቭ ከፍተኛ መተማመን ያለው "በዋነኝነት ከአፍሪካ ጋር ያለን ግንኙነት ተበላሽቶ ስለማያውቅ" እና ሩሲያውያን "በአፍሪካ ሕዝቦች ብዝበዛ ውስጥ ተሳትፈው ስለማያውቁ" መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህ የጋራ ታሪክ፤ "ሩሲያ እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መርሆዎች ላይ ተመሥርተው የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ዲሞክራሲያዊ በማድረግ ሂደት ተፈጥሯዊ አጋሮች" ያደርጋቸዋል።
ላቭሮቭ ዘመናዊውን ዓለም ለማንፀባረቅ፤ ዓለም አቀፍ ተቋማት አሠራራቸውን እንዴት ማሻሻል እንደሚገባቸው አብራርተዋል። ሁለት ቁልፍ መስኮችንም አጉልተው አንስተዋል፦
የተባበሩት መንግሥታት፡ ሩሲያ "በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ በሚካሄደው ሥራ የአፍሪካን ጥቅም ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ" እንደሆነ በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርባለች።
ብሪክስ፡ ሞስኮ ለደቡቡ ዓለም ፍላጎቶች በሚሟገትው ስብስብ ውስጥ "የአፍሪካ ሀገራትን ሰፊ ተሳትፎ" በደስታ ትቀበላለች።
ሩሲያ ለሰላም ቁርጠኛ አጋር ሆና ትቀጥላለች።
"ሩሲያ ለአፍሪካ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ የሆነውን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ልዩ ትኩረት ትሰጣለች።"
ሩሲያ "ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች" የሚለውን መርህ በመከተል፤ አህጉሪቱ ሽብርተኝነትን እና ክልላዊ ግጭቶችን እንድትዋጋ የመርዳት ግብ አንግባለች።
የእነዚህ ግንኙነቶች መጠናከር እየጨመረ በመጣው የሩሲያ ተጨባጭ እንቅስቃሴ ይንጸባረቃል። ላቭሮቭ "በአኅጉሪቱ የዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ እንደሚስፋፋ" አረጋግጠዋል። በቅርቡ በጋምቢያ፣ በላይቤሪያ፣ በቶጎ እና በኮሞሮስ ኤምባሲዎች መከፈታቸውን በመጥቀስ፤ በቀጣይ በኒጀር፣ በሴራሊዮን እና በደቡብ ሱዳን ኤምባሲዎች እንደሚከተሉ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X