ኢትዮጵያ እና ሕንድ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ሕንድ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ተፈራረሙ
ስምምነቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕንዱ አቻቸው ናሬንድራ ሞዲን በትናንትናው ዕለት በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ተቀበለው የሁለትዮሽ ውይይት ካካሄዱ በኋላ የተፈፀመ ነው፡፡ ውይይቶቹ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የጋራ የትብብር ጉዳዮችን ማስፋት እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን መመልከት ላይ ያተኮሩ እንደነበር ተገልጿል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በርካታ ስምምነቶችን የፈፀሙ ሲሆን በሚከተሉት ዘርፎች ላይ የመግባቢያ ሰነዶችን ተፈራርመዋል፦
◻ የጉምሩክ ትብብር፣
◻ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመረጃ ማዕከል ማቋቋም፣
◻ ሁለቱ ሀገራት ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ያላቸውን ቁርጠኝነት በሚያሳይ መልኩ ለተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ሥልጠና ዝግጅት፡፡
ኢትዮጵያ እና ሕንድ ግንኙነታቸውን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ የተስማሙም ሲሆን ይህም ለሁለቱ ሀገራት ትስስር አዲስ ምዕራፍ ነው ተብሏል። የሁለትዮሽ ትብብሩ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ እና በጤና ዘርፎች ላይ እንዲስፋፋ ከመግባባት መደረሱም ተጠቁሟል።
ሕንድም የሚከተሉትን እንደምትፈጽም አስታውቃለች፦
ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የሚሰጠውን የሕንድ የባሕል ግንኙነት ምክር ቤት ነፃ የትምህርት ዕድል በእጥፍ መጨመር፣
በሕንድ የቴክኒክና ኢኮኖሚ ትብብር ፕሮግራም ስር የአጭር ጊዜ የሰው ሠራሽ ክህሎት ሥልጠና ኮርሶችን ማስተዋወቅ፣
በአዲስ አበባ በሚገኘው ማህተማ ጋንዲ ሆስፒታል የእናቶችና የህፃናት ጤና አጠባበቅን መደገፍ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ይፋዊ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ ኦማን ማቅናታቸው ይታወቃል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X