የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የአዲስ አበባ እና ኒው ዴልሂን ግንኙነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ሰጥቶታል - የዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የአዲስ አበባ እና ኒው ዴልሂን ግንኙነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ሰጥቶታል - የዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የአዲስ አበባ እና ኒው ዴልሂን ግንኙነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ሰጥቶታል - የዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የአዲስ አበባ እና ኒው ዴልሂን ግንኙነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት ሰጥቶታል - የዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከወዳጅነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሸጋግር ነው ሲሉ ባለሙያው መሃመድ ሲራጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት አመልክተዋል፡፡

“አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን ሕንድ ኢትዮጵያን እንደ ስትራቴጂካዊ ሀገር ልትመለከታት ትችላለች። በተለይ አዲስ አበባን የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣናን ለመድረስ ልትጠቀምባት ትችላለች። በዲፕሎማሲውም ከኢትዮጵያ ጋር መወገን ወይንም ከኢትዮጵያ ጋር ትብብር መፍጠር ማለት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ተሰሚነት ማግኘት ሆኖ ሊወሰድ ይችላል” ብለዋል።

በሌላ በኩል ሁለቱ የብሪክስ አባል ሀገራት በስብስቡ ውስጥ የሚኖራቸው ትብብር የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ረገድ የሚጫወተውን ቁልፍ ሚናም አንስተዋል፡፡

"እንደሚታውቀው ኢትዮጵያ አዲስ የብሪክስ አባል ናት። ይሄ እንግዲህ ግንኙነቱን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ይሰጠዋል።... በዚህ ውስጥ በርካታ አዳዲስ እድሎች ይኖራሉ። በተለይ በሀገራዊ ገንዘቦች መገበያየት እና ከአዲሱ የልማት ባንክ የልማት ብድር ለማግኘት እድል ይዞ እንደሚመጣ ይታመናል።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0