ሙሉ ቪዲዮ፦ በምዕራቡ ዓለም ሥልጣኔ ሳይሆን ዝቅጠት ብቻ ነው ያለው - ፑቲን
16:03 17.12.2025 (የተሻሻለ: 16:14 17.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሙሉ ቪዲዮ፦ በምዕራቡ ዓለም ሥልጣኔ ሳይሆን ዝቅጠት ብቻ ነው ያለው - ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት በመከላከያ ሚኒስቴር የቦርድ ስብሰባ ላይ የተናገሯችው ተጨማሪ ነጥቦች፦
ሩሲያ ከሶቪዬት ኅብረት መፈራረስ በኋላ የምዕራቡ ዓለም ሙሉ አባል አልሆነችም፡፡
ሩሲያ ኔቶ ወደ ምስራቅ እንደማይስፋፋ የገባውን ቃል እንዲፈጽም በድጋሚ ትጠይቃለች፡፡
ምዕራቡ ዓለም የሩሲያን ጥያቄ ችላ በማለት ሁኔታውን ወደ ጦርነት ቀይሮታል፡፡
ምዕራቡ ዓለም እና "የአውሮፓ አሳማዎች" ሩሲያን ለማፍረስ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም፡፡
ሩሲያ በሁሉም መልኩ ሉዓላዊ ሀገር የሆነችው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነው፡፡
የሩሲያ ጦር እያደገ ነው፤ የኒውክሌር ጋሻውም ዘምኗል፡፡
ዩክሬን እንደ ሀገር እየፈራርሰች ነው፣ ይህም በሙስና ቅሌቱ እና መቶ ሺህ በሚቆጠሩ ኩብለላዎች ታይቷል፡፡
ከአውሮፓ ጋር ለመነጋገር ተስፋ እናደርጋለን ነገር ግን ይህ ከወቅቱ የፖለቲካ ልሂቃን ጋር የማይሆን ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X