የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ "ዲጂታል ብር" ለማስተዋወቅ በይፋ ጥናት ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ "ዲጂታል ብር" ለማስተዋወቅ በይፋ ጥናት ጀመረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዲጂታል ብር ለማስተዋወቅ በይፋ ጥናት ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ "ዲጂታል ብር" ለማስተዋወቅ በይፋ ጥናት ጀመረ

የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ወደ ላቀ ዲጂታል ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችለውን የማዕከላዊ ባንክ የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ ሥራ ላይ ለማዋል አስቻይነቱን የማጥናት ሥራ በይፋ መጀመሩን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ባንኩ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው መግለጫ፤ ይህ ጥናት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ግብን ዳር ለማድረስና የገንዘብ ዝውውርን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጿል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ሥራው ገና በሙከራ ላይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው፤ “ምን ማለት እንደሆነ በትክክል አናውቅም፣ ነገር ግን በእርግጠኝነት ማጥናት አለብን” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ዲጂታል ብር ከመደበኛው የወረቀት ብር ጋር እኩል ዋጋ ኖሮት እንደ ተጨማሪ አማራጭ የሚያገለግል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በብሔራዊ ባንክ ዋስትና የሚሰጠው የኤሌክትሮኒክ መገበያያ ይሆናል ተብሏል።

ባንኩ በጥናቱ የሳይበር ደህንነት፣ የግል መረጃ ጥበቃ እና ለዲጂታል ክፍያ የሚያስፈልጉ የሕግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ትኩረት የሚሰጣቸው ቀዳሚዎቹ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0