- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል።አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ እና የሩሲያ በዘመናት የተፈተነ ከጭቁኖች ጋር የመቆም ታሪክ

የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ እና የሩሲያ በዘመናት የተፈተነ ከጭቁኖች ጋር የመቆም ታሪክ
ሰብስክራይብ
“የብሪክስ መድረክ ለአባል ሀገራት የበለጠ ስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂ እና የጋራ ጥቅምን መሰረት ያድረጉ ግንኙነቶችን ለመመስረት እድል ይሰጣል። ከዚህ አናፃር የኢትዮጵያ እና የህንድ ግንኙነት ከዚህ ማዕቀፍ በእጅጉ ይጠቀማል” ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከብሪክስ አገራት ትብብር አንፃር ቀዳሚ ጉዳዩ አድርጎ ይቃኛል። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህን (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን የሶቪየት ኅብርት ለአፍሪካ የነፃነት ምን ሚና ነበራት ሲል ይጠይቃል ፣ ዛሬም ድረስ የቀጠለውን አጋርነትም በሰፊው በሰፊው እንዳስሳለን።
“ሩሲያ በታሪኳ በሙሉ በአፍሪካ ሕዝቦች ጭቆና ውስጥ ተሳትፋ አታውቅም ካለማወቋም በላይ እራሷን በዓለም ዙሪያ ለተጨቆኑ ሕዝቦች ድምፅ እንዲሁም የትግላቸው ደጋፊ ነች” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የታሪክ ተመራማሪ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerAfripods Spotify Pocket Casts Podcast Addict CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0