በደቡብ አፍሪካ ኳዙሉ-ናታል ፓርላማ ካልተሳካ የመተማማኛ ድምጽ ውሳኔ በኋላ ትርምስ ተፈጠረ

ሰብስክራይብ

በደቡብ አፍሪካ ኳዙሉ-ናታል ፓርላማ ካልተሳካ የመተማማኛ ድምጽ ውሳኔ በኋላ ትርምስ ተፈጠረ

በኳዙሉ-ናታል የክልል የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ታሚ ንቱሊ ላይ የመተማማኛ ድምፅ ማጣት ውሳኔ ቢካሂድም ውሳኔው ማለፍ እንዳልቻለ ተዘግቧል።

ከፓርላማው አጠቃላይ 80 መቀመጫዎች 37ቱን የያዙት እና ድምፅ አሰጣጡ እንዲካሄድ ያደረጉት የተቃዋሚው የኡምክሆንቶ ዌሲዝዌ ፓርቲ የሕግ አውጪዎች፤ ወደ አፈ-ጉባኤው በኃይል በመሄድ፣ ሲገፋፉ፣ በቁጣ የእጅ ምልክቶችን ሲያሳዩ እና ዕቃዎችን በመወርወር ሁከት ሲፈጥሩ እንደነበር የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ፖሊስ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን ለመበተን ጣልቃ የገባ ሲሆን፣ የፓርቲው ደጋፊዎች ደግሞ ወደ ጎዳና በመውጣት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

ገዢውን ጥምር መንግሥት የክልሉን ፋይናንስ በመበዝበዝ የከሰሰው ተቃዋሚ ፓርቲው፤ ድምጽ አሰጣጡ ቢሳካ ኖር ቁልፍ በሆነው ክልል ውስጥ ሥልጣን ሊያገኝ ይችል እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0