የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን ንብረቶች የመያዝ ዕቅድ የዩክሬን ግጭትን ለማቀጣጠል ያለመ ነው - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን ንብረቶች የመያዝ ዕቅድ የዩክሬን ግጭትን ለማቀጣጠል ያለመ ነው - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን ንብረቶች የመያዝ ዕቅድ የዩክሬን ግጭትን ለማቀጣጠል ያለመ ነው - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.12.2025
ሰብስክራይብ

የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን ንብረቶች የመያዝ ዕቅድ የዩክሬን ግጭትን ለማቀጣጠል ያለመ ነው - የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

የአውሮፓ ኅብረት ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች በሚገኘው ገንዘብ የዩክሬንን ወታደራዊ ጥረቶች ለመደገፍ እንዳሰበ የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ሲያሪቶ በብራሰልስ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

"የዛሬው ተግባር ግጭትን ማካካር ተቀባይነት እንደሌለው ግልጽ ማድረግ ነው፤ ምክንያቱም በአውሮፓ እና በሩሲያ መካከል ጦርነት ከተነሳ አውሮፓ አትተርፍም። ስለዚህ እንደዚህ አይነት ጦርነት እንዳይጀመር መከላከል አለብን" ብለዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ባሳለፈነው አርብ ታህሳስ 3፤ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ንብረቶችን በቋሚነት ለማገድ ድምጽ ሰጥቷል።

የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ይህ ውሳኔ በኅብረቱ ላይ "የማይጠገን ጉዳት" እንደሚያደርስ ከዚህ ቀደም ገልፀው ነበር።

ሃንጋሪ እና ስሎቫኪያ የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያ የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦቶችን እስከ 2028 መጀመሪያ ድረስ ሙሉ በሙሉ ለማቆም በሚያደርገው ጥረት ዙሪያ በአውሮፓ ኅብረት ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት የሕግ ዝግጅቶችን አጠናቀዋል ሲሉም ሲያሪቶ ተናግረዋል።

የሩሲያን ነዳጅ እና ጋዝ የመተው ዕቅድ የአውሮፓ ኅብረት ሕጎችን ይጥሳል ሲሉም አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0