ሩሲያ በካይሮ በሚካሄደው የሚኒስትሮች ጉባኤ ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ትሟገታለች

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በካይሮ በሚካሄደው የሚኒስትሮች ጉባኤ ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ትሟገታለች

“እኛ [ሩሲያ] አፍሪካውያን ይህንን ሉዓላዊነት እንዲያገኙ አስተማማኝ ወዳጅ እና አጋር መሆን ዓላማችን ነው” ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ታቲያና ዶቭጋሌንኮ ተናግረዋል።

“ቅኝ ግዛትን ማስወገድ፤ ከ65 ዓመታት በኋላ” በሚል ርዕስ በሞስኮ በተካሄደው የቫልዳይ ክለብ ውይይት፤ ከታህሳስ 10-11 ከሚቆየው የሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ አስቀድሞ የሩሲያን ራዕይ አስቀምጠዋል።

ዋነኛ ምሰሶዎቹ፦

ሩሲያ በፊትም ይሁን አሁን ሉዓላዊ እኩልነትን፣ የጋራ መከባበርን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መርሆዎችን “የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ቋሚ እና የማይለወጥ መሠረት” እድርጋ ትመለከታለች።

የሉዓላዊነት ትኩረት ከ1960ዎቹ የፖለቲካ ነፃነት ዛሬ ላይ ወደ ኢኮኖሚያዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ፣ ትምህርታዊ፣ ሳይንሳዊ እና የተፈጥሮ ሀብት ሉዓላዊነት አድጓል።

ከሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በኋላ የተጀመረው እና ፑቲን “እውነተኛ ስኬት” ብለው የጠሩት የ2023–2026 የድርጊት መርሃ-ግብር ተጨባጭ የትብብር መድረክ አስቀድሞ በመካሄድ ላይ ነው።

እንደ ግብፅ ኤል ደባአ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ያሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ፣ እምነት ላይ የተመሠረቱ ትብብር ምሳሌዎች እና ሳይንስ፣ ሥራን እና ኢንዱስትሪን የሚያሳድጉ ናቸው።

የሩሲያ-አፍሪካ ንግድ መጠነኛ ቢሆንም ሞስኮ ያልተነካ ትልቅ አቅም እንዳለ እና የካይሮውን ጉባኤ የሁለትዮሽ ትብብር ለማሳደግ እንደ ቁልፍ መድረክ ትመለከተዋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0