የአፍሪኤግዚም ባንክ አዲስ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ በግብፅ ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪኤግዚም ባንክ አዲስ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ በግብፅ ተጀመረ
የአፍሪኤግዚም ባንክ አዲስ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ በግብፅ ተጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.12.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪኤግዚም ባንክ አዲስ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ በግብፅ ተጀመረ

ሀሰን አላም ኮንስትራክሽን 250 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጀውን ውል ከተረከበ በኋላ የአፍሪካ የወጪ እና ገቢ ንግድ ባንክ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ በአዲሱ የግብፅ አስተዳደራዊ ከተማ ተጀምሯል፡፡

የአፍሪኤግዚም ባንክ የአፍሪካ ንግድ ማዕከል የተሰኘው ሕንፃ በአፍሪካ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር ማዕከል እንዲሆን ታስቦ የሚሠራ ነው።

ፕሮጀክቱ፦

የዋናው መሥሪያ ቤት ሕንፃ፣

110 ክፍሎች ያሉት ሆቴል፣

ስድስት የመኖሪያ ቪላዎች፣

ሰፊ የንግድ ድጋፍ ሰጪ መገልገያዎች፤ ግዙፍ የጉባኤ ማዕከል፣ የኤግዚቢሽን ቦታ እና የፈጠራ ማዕከልን ያካትታል።

"የአፍሪኤግዚም ባንክ የአፍሪካ ንግድ ማዕከል ለባንኩ መስፋፋት ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ንግዶች መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት መረጃ እጥረት ለመቅረፍም ታስቦ የሚገነባ ነው። ይህ ደግሞ ለሰባት አስርተ ዓመታት ያህል ለአፍሪካ የውስጥ ንግድ እና ኢንቨስትመንት እድገት እንቅፋት ሆኖ የቆየ ፈተና ነው" ሲሉ የባንኩ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ ተናግረዋል፡፡

በአፍሪኤግዚም ባንክ መረጃ መሠረት፤ ፕሮጀክቱ በ36 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በግንባታው ወቅት ወደ 8 ሺህ ያህል፤ ወደ መደበኛ ሥራ ሲገባ ደግሞ አንድ ሺህ ቋሚ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0