የደቡብ አፍሪካ ሪዘርቭ ባንክ የሀገሪቱን የገንዘብ ስርዓት ለማዘመን መጠነ ሰፊ ለውጥ እያደረገ እንደሆነ ተገለፀ

የደቡብ አፍሪካ ሪዘርቭ ባንክ የሀገሪቱን የገንዘብ ስርዓት ለማዘመን መጠነ ሰፊ ለውጥ እያደረገ እንደሆነ ተገለፀ
የ "ዘመነ ጥሬ ገንዘብ ስትራቴጂ" በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ገጠራማ አካባቢዎች፤ ጥሬ ገንዘብን ተደራሽ እና አቅምን ያገናዘበ በማድረግ ገንዘብን የማስተዳደር እና የመያዝ ሸክምን ለመቀነስ ያለመ እንደሆነ የአሜሪካ ሚዲያዎች የባንኩን ባለሥልጣናት ጠቅሰው ዘግበዋል።
ጥሬ ገንዘብ አሁንም ከአጠቃላይ ግብይት ውስጥ ወደ ሁለት ሦስተኛውን የሚሸፍን ሲሆን ከፍተኛው የማስተዳደር ወጪ በአብዛኛው በሸማቾች ላይ ይወድቃል።
የዕቅዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
አዲስ የገንዘብ አገልግሎት፦ ፍላጎትን መስመር ለማስያዝ እና ጥሬ ገንዘብን በብቃት ለማሰራጨት በጋራ የሚመራ የገንዘብ አስተዳደር ኩባንያ በመፍጠር ለግል ገንዘብ አከፋፋዮች የሚሰጠውን ድጎማ ማስወገድ።
ኋይት ሌብል ኤቲኤሞች፦ በባንክ የተያዙ ኤቲኤሞችን ወደ የጋራ፣ ተናባቢ አውታረመረብ በመቀየር ማንኛውም ደንበኛ አነስተኛ ወይም ምንም ክፍያ ሳይከፍል ገንዘብ ማውጣት እንዲችል ማድረግ።
የተስፋፋ ቁጥጥር፦ ደህንነትን እና ቅልጥፍናን ለማሻሻል ለገንዘብ ማጓጓዣ ኩባንያዎች እና ቸርቻሪዎች ደንቦችን እና የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓትን ማስተዋወቅ።
ባንኩ እንደ ህንድ እና ብራዚል ባሉ ሌሎች ታዳጊ ሀገራት የታየው የዲጂታል ክፍያ ደረጃ ሲያድግ የገንዘብ አጠቃቀም ከ30-40 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ይገምታል።
እስከ ሶስት ዓመታት ሊወስድ የሚችለው አዲሱ ስትራቴጂ፤ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የጥሬ ገንዘብን ሚና ለመጠበቅ ያለመ ነው።
ዕቅዱ በዚህ ወር ለባንኮች የቀረበ ሲሆን የኢንዱስትሪው ምክክሮች በጥር ወር ይጀምራሉ ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X