ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ቤዛ ኃይሉ 'አላዛር' በተሰኘ ፊልም ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ
14:39 15.12.2025 (የተሻሻለ: 14:44 15.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ቤዛ ኃይሉ 'አላዛር' በተሰኘ ፊልም ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ
በፊልም ጽሁፍ አዘጋጁና ዳይሬክተሩ የተሠራው ፊልም፤ የ "ዳካር ኮርት የ2025 ዓለም አቀፍ የአጭር ፊልም ፌስቲቫል ግራንድ ፕሪ ሽልማት አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል፡፡
ለ36 ደቂቃዎች የሚዘልቀው “አላዛር” ፊልም፣ ለምርጥ ዳይሬክተር የሚሰጠውን “አባባካር ሳም ማክሃራም” የተሰኘውን ሽልማት መቀዳጀቱንም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
ፊልሙ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የገበሬ ማህበረሰብ ሐይማኖት፣ አመክንዮ እና አምልኮ ዙሪያ በማጠንጠን ተመልካቾችን ስሜታዊ መዋዥቅ ውስጥ ሰቅዞ እንደሚይዝ ዳኞቹ ለምርጫቸው በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X