በኢራን የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሀገሪቱን የመከላከያ ዘርፍ ስኬቶች የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ ጎበኘ
13:36 15.12.2025 (የተሻሻለ: 13:44 15.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢራን የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሀገሪቱን የመከላከያ ዘርፍ ስኬቶች የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ ጎበኘ
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የተመራው የፓርላማ ልዑካን ቡድን፤ ከኢራን አቻው በቀረበለት ይፋዊ ግብዣ በሀገሪቱ የሁለትዮሽ ውይይት እና ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡
የልዑክ ቡድኑ ከኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባዔ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ ጋር በመሆን ከፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን፣ ከፍትሕ ሚኒስትሩ ጎልም-ሆሴን ሞህሰኒ ኤጄኢ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ ጋር ተገናኝቷል፡፡
🪖በጉብኝታቸው ቴህራን በመከላከያ ኢንዱስትሪ መስክ የደረሰችበትን ደረጃ አስመልክቶ ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ኢራናውያን የዘርፉ ልሂቃንና ባለሙያዎች ያበለፀጓቸውን ወታደራዊ የመከላከያ መሳሪያዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል ሲል የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X