የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ከዩሮክሊር ከ226.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ነው ሲል የሞስኮ ፍርድ ቤት አስታወቀ
12:53 15.12.2025 (የተሻሻለ: 13:14 15.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ከዩሮክሊር ከ226.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማስመለስ ጥረት እያደረገ ነው ሲል የሞስኮ ፍርድ ቤት አስታወቀ
የሩሲያ ባንክ በአውሮፓ ኅብረት የታገዱ የሩሲያ ሀብቶችን ለመውረስ በሚደረገው ጥረት ሳቢያ በአውሮፓ የተቀማጭ ገንዘብ ባንክ ዩሮክሊር ላይ ክስ መመስረቱን የሞስኮ የግልግል ፍርድ ቤት ለስፑትኒክ አስታውቋል፡፡ በቀረበው ክስ እንዲመለስ የተጠየቀው ገንዘብ ከ18 ትሪሊዮን ሩብል ($226.4 ቢሊዮን) በላይ እንደሆነም ጠቁሟል።
ቀደም ሲል የሩሲያ ባንክ በታገዱ ንብረቶች እና በስፑትኒክ ስሌት ወደ 18.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የታጣ ትርፍ ዙሪያ ካሳ ለመጠየቅ በሞስኮ ፍርድ ቤት በዩሮክሊር ላይ ክስ ለመመስረት ማቀዱን አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ኮሚሽን የሩሲያን የታገዱ ሉዓላዊ ንብረቶች ተጠቅሞ ለዩክሬን እስከ 210 ቢሊዮን ዩሮ (246.7 ቢሊዮን ዶላር) ብድር ለማግኘት የሚያስችል ሀሳብ እያራመደ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X