ፓን አፍሪካዊው ኬሚ ሴባ ‘ልታቆሙን አትችሉም’ ሲል ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣን ተቃወመ
11:39 15.12.2025 (የተሻሻለ: 11:44 15.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፓን አፍሪካዊው ኬሚ ሴባ ‘ልታቆሙን አትችሉም’ ሲል ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣን ተቃወመ
በቤኒን ለተካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ድጋፍ የሰሰጠው የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ፤ “ቅድመ ጥንቃቄ” ማድረግ ከጀመረ እንደቆየ በተንቀሳቃሽ ምሥል ባስተላለፈው መልዕክት ገልጿል፡፡
ℹ በትክክለኛው ስሙ ስቴሊዮ ጊልስ ሮበርት ካፖ ቺቺ በሚል የሚጠራው ኬሚ ሴባ፤ በተለይም “አለቃቸው” እያለ ከሚጠራቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማንሳት ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎንን በፅኑ ይተቻል።
“ፓትሪስ፤ በእኛ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥተሃል፤ ነገር ግን የተሳሳተ ጥቁር ሰው መርጠሃል። በግልፅ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም ልታቆመን አትችልም” ብሏል።
የቤኒን የኢኮኖሚ ወንጀሎች እና ሽብርተኝነት መከላከያ ፍርድ ቤት ታህሳስ 3 ቀን በተሟጋቹ ላይ ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። “በመንግሥት ደህንነት ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች፣ ጥላቻ፣ ሁከት እና አመፅ በመቀስቀስ ይቅርታ እንዲጠይቅ” ይፈለጋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X