ኢኮዋስ በምዕራብ አፍሪካ መፈንቅለ መንግሥት እና አለመረጋጋትን ለመዋጋት ዝግጁነቱን ገለፀ

ኢኮዋስ በምዕራብ አፍሪካ መፈንቅለ መንግሥት እና አለመረጋጋትን ለመዋጋት ዝግጁነቱን ገለፀ
የኢኮዋስ መሪዎች በአቡጃ በተካሄደው 68ኛ መደበኛ ጉባኤ ሕገ-መንግስታዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን መያዝን ለማስቆም፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እና ክልላዊ ደህንነትን ለማጠናከር ወሳኝ አቋም መያዛቸውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል።
ቁልፍ ውሳኔዎች እና ተግባራት፦
◻ ከማዕቀብ ወደ ቅድመ መከላከል ጣልቃገብነት ሽግግር፦ ኅብረቱ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችን መፈንቅለ መንግሥት ከተከሰተ በኋላ ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ ይጠቀማል።
◻ ፈጣን ምላሽ ተረጋግጧል፦ በቤኒን ሕዳር 28 የተሞከረውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ለማክሸፍ የናይጄሪያን የጦር ጄቶች እና ወታደሮችን በአፋጣኝ ማሰማራትን ጨምሮ የተወሰደው የጋራ እርምጃ ለክልላዊ ትብብር ምሳሌ ተብሎ ተሞካሽቷል።
◻ አዲስ የአየር ጉዞ ስምምነት፦ ከጥር 2026 ጀምሮ ኢኮዋስ የጉዞ ወጪዎችን ለመቀነስ እና የክልላዊ ውህደትን ለማሳደግ የአየር ትራንስፖርት ግብሮችን ይሰርዛል።
◻ አሊኮ ዳንጎቴ የሕዝብና የግል ሽርክናዎችን ለማስፋፋት የአዲሱ የኢኮዋስ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል።
መሪዎቹ ውስጣዊ ክፍፍል ሕብረቱን እንደሚያዳክም አጽንኦት በመስጠት፤ ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት፣ ዲሞክራሲ እና የጋራ ሉዓላዊነት ለድርድር የማይቀርቡ ጉዳዮች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ይህንን አቋም በመደገፍ፤ የቤኒንን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ "ተቀባይነት የሌለው" ሲል የገለፀ ሲሆን ለጠንካራ ዲሞክራሲያዊ ቅንጅትም ጥሪ አቀቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X