#viral | 'ከጆሎፍ* ይልቅ ለበርገር ለምን እፋለማለሁ?' – የደቡብ አፍሪካው ማሌማ የሚጠበቀው የአሜሪካ ቪዛ እገዳ አላስፈራቸውም

ሰብስክራይብ

#viral | 'ከጆሎፍ* ይልቅ ለበርገር ለምን እፋለማለሁ?' – የደቡብ አፍሪካው ማሌማ የሚጠበቀው የአሜሪካ ቪዛ እገዳ አላስፈራቸውም

“አሜሪካ ወደ ግዛቷ እንዳልገባ ብትወስንም ምንም አይደለም። ወደ ዚምባብዌ፣ ቦትስዋና ወይም ናይጄሪያ እገባለሁ፡፡ ወደ ቤቴ አፍሪካ እገባለሁ” ሲሉ የኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮች ፓርቲ መሪ በቅርቡ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።

በጠበኛ ንግግራቸው እና አሜሪካ በአፍሪካ ላይ የምትከተለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በጽኑ በመተቸት የሚታወቁትን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ንግግር ያሳየው ቪዲዮ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

*ጆሎፍ ናይጄሪያ፣ ጋና እና ሴኔጋልን ጨምሮ በምዕራብ አፍሪካ አገራት የሚዘወተር የምግብ አይነት ነው፡፡ ሩዝ በተጠበሰ የበሬ፣ በዶሮ፣ በፍየል ወይም የዓሣ ሥጋ ጋር በቲማቲም ድልህ ወዝቶ፣ በቅመማ ቅመም ጣፍጦ የሚቀርብበት ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0