ለአፍሪካውያን የሚደረግ ካሳ በአኅጉሪቱ ብልጽግናን ማስፈንና ክፉኛ የተዛቡ አመለካከቶችን ማረም አለበት - የተመድ ባለሥልጣን

ለአፍሪካውያን የሚደረግ ካሳ በአኅጉሪቱ ብልጽግናን ማስፈንና ክፉኛ የተዛቡ አመለካከቶችን ማረም አለበት - የተመድ ባለሥልጣን
የአፍሪካ ሕብረት ለጎርጎሮሳውያኑ 2025 ያወጣው የካሳ ጉዳይ ዋነኛ ትኩረት፣ ከምሳሌያዊ ማካካሻ አልፎ አሁን ያሉትን ኢ-ፍትሐዊነቶች ለመፍታት ያለመ ወደፊት ተኮር አጀንዳ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በግል አስተያየት ጽሑፋቸው አስነብበዋል።
ጋቴቴ ኢ-ፍትሐዊ የንግድ ስርዓቶችን፣ የተጋነነ የብድር ወጪዎችን እና አፍሪካ እንደ ኮኮዋ ያሉ ጥሬ ዕቃዎችን ከማቀነባበር ይልቅ እንደምትልክባቸው ያሉ ብዝበዛ የሰፈነባቸው የምርት ሰንሰለት ታሪኮች የሀብት ንጥቂያ ዘመናዊ መገለጫዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ጽሑፉ፣ የመሬት አስተዳደርን የካሳ ክርክር ማዕከል አድርጎ ካቀረበውና በኮሚሽኑ ወጪው ተሸፍኖ የተደረገው የቅርብ ጊዜ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉባኤ ተከትሎ የወጣ ነው።
ጋቴቴ ለውጥ አምጪ መንገድ የሚሏቸውን መፍትሄዎች በሚከተለው መንገድ ዘርዝረዋል፦
🟠 የመሬት ባለቤትነት መብቶችን ማረጋገጥ፦ ለኢንቨስትመንት እና ለፍትሕ መሠረት እንዲሆን ለሴቶች እና ለአነስተኛ አርሶ አደሮች የመሬት ባለቤትነትን ማጠናከር።
🟠 የኢንዱስትሪ እድገትንና እሴት መጨመር፦ አፍሪካን በዓለም አቀፍ የምርት ሰንሰለት የመጨረሻ ተርታ የሚያሰልፉ ማበረታቻዎችን ማስወገድና በራሷን ጥሬ ሀብት ላይ እሴት እንድትጨምር ማስቻል።
🟠 የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣናን መተግበር፦ ክልላዊ የምርት ሰንሰለቶችን እና ተወዳዳሪ ገበያዎችን ለመገንባት የአኅጉሪቱን የነፃ ንግድ ቀጣና መጠቀም።
🟠 ዲያስፖራውን ማሳተፍ፦ ለካፒታል፣ ለሙያዊ እውቀት እና ለማነሳሻ እንቅስቃሴዎች ከአፍሪካ ዲያስፖራ ጋር ስትራቴጂያዊ አጋርነት መፍጠር።
🟠 ዓለም አቀፍ ፋይናንስን ማሻሻል፦ ኢ-ፍትሐዊ የብድር ደረጃዎችን እና በዓመት 88 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ከአኅጉሪቱ የሚሸሹ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን መግታት።
ትክክለኛው ካሳ የሚለካው በመሬት፣ በካፒታል እና በቴክኖሎጂ ላይ ያለው ሥልጣን እንደገና በማመጣጠን፣ የአፍሪካን ሰፊ ሃብቶች ለሁሉም ብልጽግና መሠረት በማድረግ ነው ሲሉ ጋቴቴ ደምድመዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X