ናሚቢያ የአፍሪካ ትክክለኛ እና ተፈላጊ የቱሪዝም መዳረሻ ተብላ ተሰየመች

ናሚቢያ የአፍሪካ ትክክለኛ እና ተፈላጊ የቱሪዝም መዳረሻ ተብላ ተሰየመች
የአፍሪካ ቱሪዝም ቦርድ ናሚቢያን ለመምረጥ ያነሳሳው፣ የአገሪቱን በስፋት የተንጣለሉ፣ ጥቂት ሰው የሚኖርባቸው መልክዓ ምድሮች እና መሳጭ የአካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረገ ጉዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑን አስታውቋል።
ቦርዱ እንዳለው የአገሪቱ ማራኪነት የሚመነጨው ያሏትን የቱሪዝም መስህቦች ያልተበረዙ ትክክለኛ በማድረጓ ጭምር ነው።
በቦርዱ መሠረት ተጓዦች የአካባቢን ጥበቃን መሠረት ባደረገው የአገሪቱ ዘላቂ የቱሪዝም ሥነ-ዘዴ (ሞዴል) የሚማረኩ ሲሆን፤ ዘዴው የማኅበረሰብ ተጠቃሚነት እና ከፍተኛ ይዘትና ዝቅተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ልምዶችን ይተገብራል።
የአፍሪካ ቱሪዝም ቦርድ ደጋፊ የሆኑት ዩርገን ስታይንሜትዝ “ናሚቢያ የአካባቢ ጥበቃ እና ቱሪዝም እርስ በርስ የሚቃረኑ ኃይሎች እንዳልሆኑ አረጋግጣለች” ብለዋል።
የአገሪቱ ዋና ዋና መዳረሻዎች ፦
ሶሱቭሌይ፦ በናሚብ በረሃ ውስጥ የሚገኙ ታዋቂ ቀይ አሸዋማ የጥላ ደጋዎች እና ሸክላማ የእርጥበት ቦታዎች፡፡
ኤቶሻ ብሔራዊ ፓርክ፦ እንስሳት በውኃ ጉድጓዶች የሚሰበሰቡበት ቀዳሚ የዱር አራዊት መጠለያ፡፡
"ስኬለተን" የባሕር ዳርቻ፦ በረሃ ከአትላንቲክ ጋር የሚገናኝበት የሩቅ እና አስደናቂ የባሕር ዳርቻ፡፡
ዳማራላንድ ፦ በበረሃ-ተስማሚ ዝሆኖች እና በጥንታዊ የዓለት ጥበብ የታወቀ ቦታ ነው፡፡
ስዋኮፕሙንድ እና ዋልቪስ ቤይ፦ ለተለያዩ አይነት ጀብዱ የተሞላባቸው ስፖርቶች እና ለባሕር ላይ ሥነ-ምሕዳሮች አገልግሎት የሚሰጡ የባሕር ዳርቻ ማዕከሎች ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



