ተመድ በሱዳን የሎጂስቲክስ ማዕከሉ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 6 ሰላም አስከባሪዎች መሞታቸውን እና 8 መቁሰላቸውን አስታውቋል
14:05 14.12.2025 (የተሻሻለ: 14:14 14.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ተመድ በሱዳን የሎጂስቲክስ ማዕከሉ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 6 ሰላም አስከባሪዎች መሞታቸውን እና 8 መቁሰላቸውን አስታውቋል
የመንግሥታቱ ድርጅት ድርጊቱን የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችልም ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡
በትናትናው ዕለት በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ካዱግሊ በሚገኘው የተመድ የሎጂስቲክስ ማዕከል ላይ በደረሰው የድሮን ጥቃት የሞቱት እና የተጎዱት በሙሉ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በአብዬ ለተሰማራው የተመድ ተልዕኮ የሚያገለግሉ ባንግላዴሻውያን አባላቱ ነበሩ።
የተመድ ዋና ጸሐ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "አሰቃቂውን የድሮን ጥቃት በፅኑ አወግዛለሁ" ሲሉ ለባንግላዴሻውያን እና ለሟቾች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል። "የተመድ ሰላም አስከባሪዎችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የጦር ወንጀል ሊሆኑ ይችላሉ።"
የተመድ የሰላም ማስከበር ኃላፊ ዣን ፒየር ላክሮዋም ይህንን አሰተጋብተው "የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ዒላማ አይደሉም" ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።
ይህ ጥቃት ከዚህ ቀደም አማፂያኑ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎች ሕዳር 25 ቀን በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት በካሎጊ ከተማ በመዋዕለ ሕፃናት እና ሆስፒታል ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽመው እንደነበር ከተዘገበ በኋላ የመጣ ነው፡፡ እንደ ሱዳን ባለሥልጣናትመረጃ፣ 43 ሕጻናትን ጨምሮ 79 ሲቪሎች ተገድለዋል።
ጉቴሬዝ ውጊያ ላይ ባለው የሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ወደ ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲመለሱ ከዚህ በፊት ያቀረቡትን ጥሪያቸውን ደግመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X