ሊቢያ ከ14 ዓመታት በኋላ ብሔራዊ ሙዚየሟን ለጎብኚዎች ክፍት አደረገች
19:42 13.12.2025 (የተሻሻለ: 19:54 13.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሊቢያ ከ14 ዓመታት በኋላ ብሔራዊ ሙዚየሟን ለጎብኚዎች ክፍት አደረገች
ቀይ ግንብ (ቤተ መንግሥት) በመባልም የሚታወቀው የአገሪቱ ትልቁ ሙዚየም፣ የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊን ከሥልጣን ካስወገደው እ.ኤ.አ. ከ2011 ዓመፅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትሪፖሊ ውስጥ ለሕዝብ ዕይታ ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አል-ድበይባህ በመልሶ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ “የቀይ ግንብ መከፈት ሊቢያ ተቋሞቿን እየገነባች መሆኑን የሚያሳይ ሕያው ምስክር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
በኔቶ የሚደገፍ ግጭት በነበረበት ጊዜ የተዘጋው ይህ የባሕል መዘክር፣ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 2023 ጀምሮ እድሳት ሲደረግለት ቆይቷል።
አንድ ባለሥልጣን ለእንግሊዝ ሚዲያ እንደተናገሩት፣ ጋዳፊ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ባለሥልጣናት 21 የተዘረፉ ቅርሶችን አስመልሰዋል፤ ተጨማሪ ቅርሶችን ከውጭ የማስመለስ ጥረትም እየተደረገ ነው።
የመከፈቻ ሥነ ስርዓቱ፣ በትምህርት ቤት ጉብኝቶች መርሃ ግብር የሚጀምር ሲሆን፣ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ አንስቶ ሙሉ ለሙሉ ለሕዝብ እይታ ክፍት እንዲደረግ እቅድ ተይዞለታል።
ይህ የሆነው ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከሊቢያ አምስት የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ስፍራዎች መካከል አንዱ አደጋ ላይ ከሚገኙት ዝርዝር ውስጥ ከተወገደ በኋላ ነው።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ 
