ከ60 በላይ ሆስፒታሎች በዲጂታል ጤና ኔትዎርክ እና በክላውድ መድረኮች ውስጥ መዋሃዳቸው ተገለፀ
16:54 13.12.2025 (የተሻሻለ: 17:04 13.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከ60 በላይ ሆስፒታሎች በዲጂታል ጤና ኔትዎርክ እና በክላውድ መድረኮች ውስጥ መዋሃዳቸው ተገለፀ
በተጨማሪም 200 የጤና ተቋማት የተቀናጀ የዲጂታል ጤና ኔትዎርክና የክላውድ መድረኮችን እንዲቀላቀሉ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀርላ አብዱላሂ አስታውቀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚመሩ የጤና አገልግሎቶች ደህንነታቸው፣ ግላዊነታቸው እና ጥራታቸው የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ጠንካራ የሕግና የፖሊሲ ማዕቀፎች እየተዘረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ቴክኖሎጂው አሁን ላይ የመረጃ ትክክለኛነትን በማሻሻል፣ የተሻለ ክሊኒካዊ ውሳኔን በመደገፍ እንዲሁም በሽታዎችን አስቀድሞ በማወቅና የጤና ትንበያዎችን በማሻሻል ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያሳየ ነው ማለታቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X