ዩሮክሊር ከጎርጎሮሳውያኑ የካቲት 2022 ጀምሮ በእግድ ላይ ካሉት የሩሲያ ሀብቶች 18.8 ቢሊዮን ዶላር አግኝቷል - የስፑትኒክ ስሌቶች
15:44 13.12.2025 (የተሻሻለ: 17:34 13.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዩሮክሊር ከጎርጎሮሳውያኑ የካቲት 2022 ጀምሮ በእግድ ላይ ካሉት የሩሲያ ሀብቶች 18.8 ቢሊዮን ዶላር አግኝቷል - የስፑትኒክ ስሌቶች
በቤልጂየም የገንዘብ ማሰቀመጫ ተቋም መረጃ ላይ በመመስረት በስፑትኒክ በተሠራው ስሌት መሠረት፣ ከታገዱ የሩሲያ ሀብቶች ዓመታዊ ገቢው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በዚህም፡-
በ2022 - 821 ሚሊዮን ዩሮ (964.4 ሚሊዮን ዶላር)
በ2023 - 4.4 ቢሊዮን ዩሮ (5.16 ቢሊዮን ዶላር)
በ2024 - 6.9 ቢሊዮን ዩሮ (8.1 ቢሊዮን ዶላር) እንዲሁም
በ2025 -የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት፣ 3.9 ቢሊዮን ዩሮ (4.6 ቢሊዮን ዶላር) ሆናል።
አብዛኛው ገቢ፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ 8.9 ቢሊዮን ዩሮ (10.5 ቢሊዮን ዶላር)፣ የመጣው ከታገደው የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሀብት ነው። ዩሮክሊር በአሁኑ ወቅት በግምት 180 ቢሊዮን ዩሮ (211.4 ቢሊዮን ዶላር) የሚያወጡ የታገዱ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሀብቶችን ይዟል።
በምላሹም፣ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የታገዱትን፣ መጠባበቂያዎች እና የጠፋውን ትርፍ ለማካካስ በሞስኮ የግልግል ፍርድ ቤት በዩሮክሊር ላይ ክስ ለመመስረት ማቀዱን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X