አዲስ አበባ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ376 ሺህ በላይ የውጭ ጎብኚዎችን አስተናግዳለች ተባለ
12:49 13.12.2025 (የተሻሻለ: 12:54 13.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ376 ሺህ በላይ የውጭ ጎብኚዎችን አስተናግዳለች ተባለ
የጎብኚዎቹ ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ36 ሺህ ጎብኝዎች ብልጫ እንዳሳየ እንዲሁም ከተማዋ 2.2 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ማስተናገዷን የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታውቋል።
የጎብኚዎች ቁጥር ለመጨመሩ የከተማ አስተዳደሩ የመሠረተ ልማት ማሻሻያ እና በመላው ከተማዋ የተለያዩ የጎብኚዎች መዳረሻዎች ግንባታ አስታዋፆ አለው እንዳለው ኮሚሽነሩ ከበደ ሁንዴ ተናግረዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ኮሚሽነሩ አጠቃላይ የቱሪስት እንቅስቃሴው ወደ 61 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ አስገኝቷል፤ ይህም ለከተማዋ ኢኮኖሚ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X