- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የውጭ እርዳታ መቀነስ፡ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ ተስፋና ስጋት

የውጭ እርዳታ መቀነስ፡ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ ተስፋና ስጋት
ሰብስክራይብ
“የውጭ እርዳታ ማጣት በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው […] ለቲቢ፣ ኤች አይ ቪ እና ወባ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን ግዥ ያለ እርዳታው በተግባር የማይቻል ነው። ነገር ግን አርቀን ስንመለከት ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይችላል። ለአፍሪካ ለቲቢ፣ ኤች አይ ቪ ወይም ጤና ብቻ ሳይሆን ለእርሻ፣ ትምህርት እና ሌሎችም ሀብትን በማሰባሰብ በራሷ ላይ ለመደገፍ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።” ሲሉ የ 'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ዳይሬክተር እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በቲቢ በሽታ ከፍተኛ ጫና ካለባቸው አገሮች መካከል የሆነችው ኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ሥርዓቷ ዋነኛ የጀርባ አጥንት የነበረው የውጭ እርዳታ እየቀነሰ በመምጣቱ ወሳኝ ወቅት ላይ ትገኛለች። ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ የቲቢ ቁጥጥር ጥረቶችን ማለትም ምርመራን፣ ሕክምናን እና የመድኃኒት መቋቋምን አደጋ ላይ እየጣለ ነው። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ከ'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ዳይሬክተር እንዳልካቸው ፍቃዱ ጋር በመሆን የጤና በጀት ቅነሳ በኢትዮጵያ የሳንባ ነቀርሳ ህክምና ላይ የሚያሳድረውን ተጨባጭ ተፅዕኖ ዳስሰናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ :

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0