የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያ ዜጎች የሰጠውን ጊዜያዊ ሕጋዊ ፈቃድ እያቋረጠ መሆኑን ዛሬ ባወጣው ማስታወሻ አረጋገጠ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያ ዜጎች የሰጠውን ጊዜያዊ ሕጋዊ ፈቃድ እያቋረጠ መሆኑን ዛሬ ባወጣው ማስታወሻ አረጋገጠ
የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያ ዜጎች የሰጠውን ጊዜያዊ ሕጋዊ ፈቃድ እያቋረጠ መሆኑን ዛሬ ባወጣው ማስታወሻ አረጋገጠ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.12.2025
ሰብስክራይብ

የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያ ዜጎች የሰጠውን ጊዜያዊ ሕጋዊ ፈቃድ እያቋረጠ መሆኑን ዛሬ ባወጣው  ማስታወሻ አረጋገጠ

​የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ክርስቲ ኖኤም በፌዴራል መዝገብ ላይ በተለጠፈ ማስታወሻ ላይ እንዳሉት፣ "የአገሪቱን ሁኔታ ከገመገምን እና ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግሥት ኤጀንሲዎች ጋር ከተማከርን በኋላ፣ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ለጊዜያዊ ከለላ ደረጃ (ቲፒኤስ) ብቁ የሚያደርጋትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት እንደማትቀጥል ተወስኗል።"

ቲፒኤስ ጊዜያዊ የከለላ ደረጃ፣ በአገራቸው በሰላም መመለስ እንደማይችሉ ሲወሰን፣ በአሜሪካ ውስጥ ለሚገኙ የሌላ አገር ዜጎች ጊዜያዊ የስደተኛነት መብት ለመስጠት ለአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር ሥልጣን የሚሰጥበት አሠራር ነው።

​ቲፒኤስ የትጥቅ ግጭቶች፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ወይም ሌሎች ያልተለመዱ ሁኔታዎች ላጋጠሟቸው አገራት የሚተገበር አሰራር ነው።

በቅርብ ወራት፣ አስተዳደሩ ሄይቲን፣ ምያንማርን፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ሶሪያን እና ቬንዙዌላን ጨምሮ ከበርካታ አገራት ለመጡ ስደተኞች ከለላውን አስወግዷል። በሕዳር ወር ደግሞ ትራምፕ በሚኒሶታ ለሚኖሩ ሶማሌያውያን የሚሰጠው ከለላ ማቋረጡን አስታውቀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0