ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት አባልነት መውጣቷን አስታወቀች
16:16 12.12.2025 (የተሻሻለ: 16:24 12.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት አባልነት መውጣቷን አስታወቀች
ኤርትራ ከድርጅቱ ለመውጣት የወሰነችውን ውሳኔ በይፋ ለኢጋድ ዋና ጸሐፊ አሳውቃለች ሲል የአገሪቱ የኢንፎሜሽን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡
ኤርትራ እ.አ.አ. 1993 የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እንደገና ሲደራጅ ጀምሮ ቁልፍ ሚና መጫወቷን ያስታወሰው መግለጫው፣ ጥምረቱ በሂደት የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የማያሳካ ሆኗል ይላል፡፡
“ከጎርጎሮሳውያኑ 2005 ዓ.ም ወዲህ፣ ኢጋድ የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የሚያሟላ ሳይሆን፣ ጉዳት የሚያስከትል ሚና ተጫውቷል፡፡ በተለይም ኢላማ ለተደረጉ አባል አገራት፣ኤርትራ ላይ በልዩ ሁኔታ መሣሪያ ሆኗል። እነዚህ ያልተገቡ ድርጊቶች ኤርትራን እ.አ.አ. ሚያዚያ 2007 አባልነቷን እንድታግድ አስገድዷታል።” ብሏል መግለጫው፡፡
ኤርትራ ድርጅቱ ስህተቶቹን ያርማል በሚል ተስፋ እ.አ.አ. ሰኔ 2023 አባልነቷን ማስቀጠሏን የጠቀሰው መግለጫው፣ ኢጋድ በሕግ የተሰጡትን ግዴታዎች ባለመወጣት ይከሳል።
የኤርትራ የኢንፎሜሽን ሚኒስቴር “በዚህ ሁኔታ አንጻር ኤርትራ ሕጋዊ ሥልጣኑን እና ኃላፊነቱን ካጣ፣ ለሁሉም አባላቱ የሚታይ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ከማያስገኝ እንዲሁም ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽኦ ካላደረገ ድርጅት አባልነቷን ለማቋረጥ ተገድዳለች።” ብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X