ፑቲን ከቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ማዱሮ ጋር ተወያዩ
18:47 11.12.2025 (የተሻሻለ: 18:54 11.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፑቲን ከቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ማዱሮ ጋር ተወያዩ
ከቬንዙዌላ ሕዝብ ጋር ያላቸውን አጋርነት እና እያየለ በመጣው የውጭ ጫና ወቅት፣ የማዱሮ መንግሥት ብሔራዊ ጥቅምን እና ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የተከተለውን አካሄድ እንደሚደግፉ ገልፀዋል፡፡
የአገራት መሪዎቹ፣ በተጨማሪም በሕዳር ወር ገቢራዊ በተደረገው ስትራቴጂካዊ አጋርነት እና የትብብር ስምምነት ጋር በተጣጣመ መልኩ ወዳጃዊ የሩሲያ እና የቬኔዙዌላን ግንኙነትን በተመለከተም ሐሳብ ተለዋውጠዋል።
በንግድና ኢኮኖሚ፣ በኢነርጂ፣ በፋይናንስ፣ በባሕልና ሰብአዊ ዕርዳታና ሌሎች ዘርፎች ላይ የጋራ ፕሮጀክቶችን በተከታታይ ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ ቁርጠኝነታቸውንም አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X