ፑቲን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጠና ስላለው ሁኔታ በክሬምሊን ስብሰባ አደረጉ
17:27 11.12.2025 (የተሻሻለ: 17:34 11.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፑቲን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጠና ስላለው ሁኔታ በክሬምሊን ስብሰባ አደረጉ
የስብሰባው ዋና ዋና ነጥቦች፦
የስብሰባው ዋነኛ ትኩረት በዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ባለው ሁኔታ ላይ እንደነበር የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ሴቨርስክ ከተማ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ የጦር ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ስለመግባቷ ዝርዝር ሪፖርቶች ተቀብለዋል፡፡ ዩክሬን ሴቨርስክን የምትፈልግበት ምክንያት ለጦር ኃይሎቿ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ስላላት ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ወደ ሊማን እና ስሎቭያንስክ የሚወስደውን መንገድ የምትሸፍን ከተማ በመሆኗ ነው። ስሎቭያንስክ በዶንባስ በኪዬቭ ቁጥጥር ሥር የነበረች ግዙፍ የከተሞች ማዕከል ነች።
ፑቲን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጠና ውስጥ በሁሉም ግንባሮች ላይ አዎንታዊ ግስጋሴ መኖሩን ገልጸዋል።
ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን አስመልክቶ ስፑትኒክ ያዘጋጀውን ትንታኔ ያንብቡ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X