የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአዳማ–አዋሽ የፍጥነት መንገድ ምዕራፍ ሁለት ግንባታ የ184 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አቀረበ
17:09 11.12.2025 (የተሻሻለ: 17:14 11.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአዳማ–አዋሽ የፍጥነት መንገድ ምዕራፍ ሁለት ግንባታ የ184 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አቀረበ
ይህ የፋይናንስ ድጋፍ ኢትዮጵያ –ጅቡቲ–ደቡብ ሱዳን የትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት ላይ የሚገኘውን ከመልካ ጂሎ አዋሽ ድረስ ያለውን 67 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ ለመጀመር ያስችላል።
ይህ የትራንስፖርት መስመር ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያ የባሕር ንግድ የሚያስተናገድ ሲሆን፣ ለአገር አቀፍ የሎጂስቲክስ ፍሰት፣ ለቀጣናዊ ትስስር እና በአፍሪካ ቀንድ ለሚደረገው ኢኮኖሚያዊ ውህደት ወሳኝ መሆኑን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ባንኩ ከአገሪቱ ጋር ያለውን ስትራቴጂያዊ ትብብር ለማጠናከር በሚከተሉት ዘርፎች ቁርጠኛ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
የአገሪቱን የሪፎርም አጀንዳ ለማስቀጠል የሚረዳ የበጀት ድጋፍ በማቅረብ፡፡
ለግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ማቅረብ፣ በተለይም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢሾፍቱ ሜጋ ኤርፖርት እንዲሁም
በቁልፍ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ በማድረግ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X