ከደቡባዊ ዓለም አገራት የተውጣጡ 3,400 የሚሆኑ ወጣቶች በ10ኛው ዓለም አቀፍ የክሬምሊን በጎ አድራጎት ካዴት ቦል* ተሳተፉ

ከደቡባዊ ዓለም አገራት የተውጣጡ 3,400 የሚሆኑ ወጣቶች በ10ኛው ዓለም አቀፍ የክሬምሊን በጎ አድራጎት ካዴት ቦል* ተሳተፉ
የነፃ መንግሥታት ኮመንዌልዝ፣ የምሥራቅ እስያ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የላቲን አሜሪካ እና የበርካታ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች በታላቁ የአርበኝነት ጦርነት ድል 80ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ለማክበር እና ልዩ ወታደራዊ ዘመቻን ለመደገፍ በተደረገው በዚህ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።
ከአፍሪካ የተወከሉት አገራት የሚከተሉት ናቸው፦
ኢትዮጵያ፣
አልጄሪያ፣
ግብፅ፣
ጋና፣
ጊኒ፣
ቦትስዋና፣
ዛምቢያ፣
ካሜሩን፣
የኮንጎ ሪፐብሊክ፣
ኮትዲቯር፣
ማዳጋስካር፣
ማላዊ፣
ሞዛምቢክ፣
ቻድ፣
ቱኒዚያ እና
ናይጄሪያ ይገኙበታል።
በዚህ ዝግጅት ላይ ከ62 አገራት የተውጣጡ 272 ወጣቶችም ታድመዋል።
ዓለም አቀፉ የክሬምሊን የበጎ አድራጎት ካዴት ቦል የሩሲያን ባሕላዊና ታሪካዊ ቅርስ ለማነቃቃትና ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም በወደፊት የአባት አገር ተከላካዮች መካከል አንድነትን ለማጠናከር ታስቦ በየዓመቱ የሚደረግ አገር ወዳድነትን የሚያንጸባርቅ ትልቅ ዝግጅት ነው።
*ካዴት ቦል፡- የሠልጣኝ ወታደሮች መደበኛ ወታደራዊ መሰል ማኅበራዊ ዝግጅት ነው፡፡ ማኅበረሰባዊ ወግ መከወኛ ዕድል በመስጠት ክብርን፣ ሥነ-ምግባር እና አብሮነትን የማስተማሪያ መድረክ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X



