ዘለንስኪ ለዩክሬን ዕልባት አስፈላጊነታቸው አብቅቷል - የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዘለንስኪ ለዩክሬን ዕልባት አስፈላጊነታቸው አብቅቷል - የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ
ዘለንስኪ ለዩክሬን ዕልባት አስፈላጊነታቸው አብቅቷል - የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.12.2025
ሰብስክራይብ

ዘለንስኪ ለዩክሬን ዕልባት አስፈላጊነታቸው አብቅቷል - የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ

የዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን ምርጫ ማካሄድ አለባት የሚለው መግለጫ፣ የዘለንስኪ ሚና እያበቃ መሆኑን እና ስምምነት ላይ ለመድረስ ከሕጋዊ ቅቡልነት አንፃር አያስፈልጉም የሚል መልዕክት ያስተላልፋል፤ ሲሉ የሊባኖስ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ የሆኑት ቢሻራ ሳሊባ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ሳሊባ በሰጡት አስተያየት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው

የዘለንስኪ ሚና የሚያበቃው በሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ አማካይነት ወይም በዘመቻው መቀጠል ሊሆን ይችላል።

የአሜሪካ አስተዳደር የዩክሬን ግጭት እንዲያበቃ ይፈልጋል፤ ነገር ግን አውሮፓ ዋናው እንቅፋት ናት ምክንያቱም ለራሷ የሚመች ሁኔታ ለመፍጠር በጊዜ ለውጦች ላይ ተስፋ በማድረግ ላይ ነች።

ግጭቱ ካበቃ ዋና ተሸናፊዋ አውሮፓ ትሆናለች፣ አሁን ያለው ሁኔታ "አውሮፓውያን ቢያንስ የተወሰነ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ ወይም ጂኦፖለቲካዊ ጥቅም እንዲያገኙ የመጨረሻ ዕድላቸው" ነው።

ሳሊባ በተጨማሪም በአዲሱ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ስትራቴጂው "አውሮፓ ወደደፊት በሚከሰቱ ግጭቶች፣ በኃይል ሚዛኖች እና በፖለቲካ-ኢኮኖሚያዊ ጥምረቶች ውስጥ ያለባትን ቦታ እንደገና እንድትገልጽ" እና ፖሊሲዋን ወደ ተጨባጭ ግንኙነቶች እንድታዞር ጥሪ ያቀርባል።

ዓለም አቀፍ ልሂቃን፣ አጋርነት መመሥረት ያለበት ተመሳሳይ ትክክለኛ አቅም ካላቸው አካላት ጋር መሆን አለበት የሚል እምነታቸው እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአውሮፓ ሕብረት ሥርዓት በአውሮፓ ውስጥ የሞራል፣ የባህል፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እሴቶችን አፍርሷል፤ "የአውሮፓ መሪዎችን ወደ ማግለል እና ተፅኖቸው እንዲዳከም" አድርጓል ሲሉ ቢሻራ ሳሊባ ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0