ኢትዮጵያና ዛምቢያ በወታደራዊ መስክ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
19:52 10.12.2025 (የተሻሻለ: 19:54 10.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ዛምቢያ በወታደራዊ መስክ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከዛምቢያ አቻቸው ጄፍሪ ዚኤሌ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ፣ በደኅንነት፣ በወታደራዊ ትምህርትና ሥልጠና፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪና በሌሎችም ዘርፎች በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ለቀጣናው ደኅንነት እንዲሁም ለሀገራት ሠላምና መረጋጋት ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሠራ ፊልድ ማርሻሉ ገልፀዋል፡፡
ኤታማዦር ሹሙ ጄፍሪ ዚኤሌ በበኩላቸው “በልዩ ልዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ ለመሥራት ዛምቢያ ያቀረበችውን ጥያቄ ኢትዮጵያ በመቀበሏ ደስተኛ ነን” ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia