የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ አደረገ
19:24 10.12.2025 (የተሻሻለ: 19:34 10.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ አደረገ
ሚኒስቴሩ ከዛሬ ታህሳስ 1፣ 2018 6:00 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ይፋ ባደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የቤንዚን፣ የኬሮሲን እና የነጭ ናፍጣ ዋጋ በተመሳሳይ 129.12 ብር እንዲሆን መወሰኑን በደብዳቤው አስታውቋል፡፡
ይፋ በሆነው የዋጋ ዝርዝር መሠረት በነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ባለፈው ወር ከነበረው እስከ 8 ብር የሚደርስ ጭማሪ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
የአውሮፕላን፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ እና የቀላል ጥቁር ናፍጣ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X