ሩዋንዳ የምስራቃዊ ኮንጎ ግጭትን ወደ ክልላዊ የትጥቅ ጦርነት ለመቀየር እና ቡሩንዲን ወደ ግጭቱ ለመሳብ ትሻለች - የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩዋንዳ የምስራቃዊ ኮንጎ ግጭትን ወደ ክልላዊ የትጥቅ ጦርነት ለመቀየር እና ቡሩንዲን ወደ ግጭቱ ለመሳብ ትሻለች - የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትር
ሩዋንዳ የምስራቃዊ ኮንጎ ግጭትን ወደ ክልላዊ የትጥቅ ጦርነት ለመቀየር እና ቡሩንዲን ወደ ግጭቱ ለመሳብ ትሻለች - የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.12.2025
ሰብስክራይብ

ሩዋንዳ የምስራቃዊ ኮንጎ ግጭትን ወደ ክልላዊ የትጥቅ ጦርነት ለመቀየር እና ቡሩንዲን ወደ ግጭቱ ለመሳብ ትሻለች - የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትር

የቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኞ እለት በሰጡት መግለጫ፤ ሩዋንዳ በሕዳር 23 ግዛቷን በመድፍ እንደመታች እና በምስራቅ ኮንጎ የሚገኙ ወታደራዊ ቦታዎቿን እንዳጠቃች በመጥቀስ ክስ አቅርበዋል።

ኤም 23 በጥር ወር በምስራቅ ኮንጎ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ጎማ እና ቡካቩ ከተማዎችን መቆጣጠራቸው፤ ለበርካቶች መፈናቀል እና ለምግብ ዋስትና መባባስ ምክንያት ሆኗል። በሐምሌ 22 የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲሁም በኳታር ህዳር 6 የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ ቢፈረምም በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኃይሎች እና በኤም23 ታጣቂዎች መካከል ውጊያው እንደቀጠለ ነው።

በዚህም ከኪንሻሳ ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት የቡሩንዲ የጦር ኃይሎች ኤም23ን ጨምሮ የታጠቁ ቡድኖችን በጋራ ለመዋጋት በኮንጎ ግዛት ውስጥ ተሠማርተዋል።

የሩዋንዳ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰኔ 20 ቀን በዋሽንግተን የፈረሙት የሰላም ስምምነት፦

ሩዋንዳ ወታደሮቿን እንድታስወጣ፣ ኤም23ን መደገፍ እንድታቆም እና ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱን እንድታመቻች፤

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሩዋንዳ ነፃ አውጪ የዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ቡድንን ትጥቅ እንድታስፈታ ያስገድዳል።

ይፋዊ የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ሕዳር 25 ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሰኬዲ በደቡብ ኪቩ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሩዋንዳ ስምምነቱን ጥሳለች ሲሉ ከሰዋል። ሩዋንዳ በበኩሏ ኮንጎ የሩዋንዳ ነፃ አውጪ የዲሞክራሲያዊ ኃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት አለመቻሏ ዋናው እንቅፋት እንደሆነ ገልጻለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0