ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ መስፈርቶችን በማክበር የኒውክሌር ልማቷን ተግባራዊ ታደርጋለች - ተመስገን ጥሩነህ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ መስፈርቶችን በማክበር የኒውክሌር ልማቷን ተግባራዊ ታደርጋለች - ተመስገን ጥሩነህ
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ መስፈርቶችን በማክበር የኒውክሌር ልማቷን ተግባራዊ ታደርጋለች - ተመስገን ጥሩነህ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.12.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ መስፈርቶችን በማክበር የኒውክሌር ልማቷን ተግባራዊ ታደርጋለች - ተመስገን ጥሩነህ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜካኤል ቹዳኮቭ ጋር በኒውክሌር ትብብር ዙሪያ ማክሰኞ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይልና ቴክኖሎጂን ለንጹህ ኢነርጂ፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪና ለምርምር ልህቀት መጠቀም እንደምትፈልግ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቅርቡ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን በማቋቋምም በይፋ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መስፈርቶችና መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ትተገብራለች” ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሜካኤል ቹዳኮቭ በበኩላቸው፤ ኤጀንሲው ኢትዮጵያ ከኒውክሌር ኃይል ስትራቴጂካዊ ተጠቀሚነቷን ለማረጋገጥ የጀመረችውን ጉዞ እውን ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0