የአፍሪካ ሀገራት ክፍያዎችን ለመፈጸም በሌሎች ሀገራት ገንዘቦች ላይ ጥገኛ በመሆናቸው በእጅጉ እየተፈተኑ ነው ተባለ
14:00 10.12.2025 (የተሻሻለ: 14:04 10.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት ክፍያዎችን ለመፈጸም በሌሎች ሀገራት ገንዘቦች ላይ ጥገኛ በመሆናቸው በእጅጉ እየተፈተኑ ነው ተባለ
ሀገራቱ ከራሳቸው ብሔራዊ ገንዘቦች ይልቅ በሌሎች ሶስተኛ ሀገራት ገንዘቦች ላይ ጥገኛ መሆናቸው፤ በክፍያዎች አፈጻጸም ረገድ ከባድ ችግርን እየፈጠረ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርዓቶች ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ዳምጠው ተናግረዋል።
▫ በመሆኑም ክፍያዎችን በራሳቸው ብሔራዊ መገበያያ ገንዘቦች ሊፈጸሙ እና አህጉር አቀፍ የክፍያ ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የዲጂታል ፋይናንስ ጉባኤ፤ በአፍሪካ ድንበር ዘለል የክፍያ መንገዶችና ችግሮች ዙሪያ አተኩሮ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ፤ የተበጣጠሱ መዋቅራዊ የቴክኒክ እና የቁጥጥር ስርዓቶች መኖር በአህጉሪቱ የተዋጣለት የክፍያ ስርዓት ለመዘርጋት እንዳላስቻለ ተነስቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X