የኃይል ፍላጎታችንን ለማሟላት በአፍሪካዊ ተቋማት የሚመራ አህጉራዊ ትብብር ያስፈልገናል - አደም ፋራህ
10:31 10.12.2025 (የተሻሻለ: 10:34 10.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኃይል ፍላጎታችንን ለማሟላት በአፍሪካዊ ተቋማት የሚመራ አህጉራዊ ትብብር ያስፈልገናል - አደም ፋራህ
የመጀመሪያው የአፍሪካ የኃይል ብቃት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባኤውን የከፈቱት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ “አፍሪካ የኃይል ፍላጎቷን ለማሟላት የራሷን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ እና በራሷ ተቋማት የሚመራ አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር ይኖርባታል” ብለዋል፡፡
"አህጉራዊ ትብብር የኃይል ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት አስፈላጊ ነው። ለዚህም በአፍሪካ ተቋማት የሚመሩ መፍትሄዎችን ማመንጨት ተገቢ ነው፡፡"
ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል፣ ሥነ-ምህዳሮችን ወደነበሩበት በመመለስ፣ ተፋሰሶችን በመጠበቅ እና በማልማት ብሔራዊ የአየር ንብረት መቋቋሚያ መርሃ-ግብሯን አጠናክራ አረንጓዴ እና አካታች ኢኮኖሚ እየገነባች እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


