የናይጄሪያ ሴኔት ፕሬዝዳንቱ ወታደሮችን ቤኒን ውስጥ ለማሠማራት ያቀረቡትን ጥያቄ አጸደቀ

ሰብስክራይብ

የናይጄሪያ ሴኔት ፕሬዝዳንቱ ወታደሮችን ቤኒን ውስጥ ለማሠማራት ያቀረቡትን ጥያቄ አጸደቀ

ፕሬዝዳንት ቲኑቡ ለሕግ አውጪዎች በላኩት ደብዳቤ፤ የቤኒን ባለሥልጣናት "ሕገ-መንግሥታዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን የመያዝ እና የዴሞክራሲ ተቋማትን የማፍረስ ሙከራ" መደረጉን ተከትሎ፤ ከናይጄሪያ የጦር ኃይሎች "ልዩ እና ፈጣን የአየር ድጋፍ" ጠይቀዋል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪም ጥያቄውን ከብሔራዊ መከላከያ ምክር ቤት ጋር ከመከሩ በኋላ እንዳቀረቡት አስረድተው፤ የናይጄሪያን ክልላዊ ኃላፊነቶች እና ከቤኒን ጋር ያላትን ፅኑ ግንኙነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

"ይህ ትክክለኛ እርምጃ ነው ብለን ስለምናምን ነው። ስለዚህ የስምምነት ደብዳቤው ወዲያውኑ ለፕሬዝዳንቱ ይላካል ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ቲኑቡ፤ በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ካላት ናይጄሪያ ጋር ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ድንበር በምትጋራው ቤኒን፤ መረጋጋትን ለመደገፍ ሕግ አውጪዎች "በፍጥነት" እርምጃ እንዲወስዱም አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0