ፈረንሳይ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት ለማፈን ረድታለች - የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ

ፈረንሳይ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት ለማፈን ረድታለች - የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ
ፓሪስ ሁኔታውን በማረጋጋት ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውታለች ሲሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመጀመሪያዎቹ ሰዓታት ጀምሮ ስለተፈጠሩት ክስተቶች መረጃ እንደተሰጣቸው እና የፈረንሳይን ድጋፍ ለማረጋገጥ ፓትሪስ ታሎንን በስልክ እንዳነጋገሩም ተገልጿል።
ማክሮን የፈረንሳይ ልዩ ኃይል አባላት በኮቶኑ በተጠንቀቅ ቆመው እንደነበር እና የፈረንሳይ የስለላ አገልግሎቶችም በኢኮኖሚ ከተማዋ ላይ ተደጋጋሚ የስለላ በረራዎችን ጨምሮ ተግባራዊ እገዛ አድርገዋል ብለዋል።
በሌላ በኩል፤ ማክሮን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በአፋጣኝ ወታደራዊ ጣልቃገብነት እንዲጀምሩ በማሳሰባቸው፤ የአየር ጥቃት እና የእግረኛ ወታደሮች ስምሪት መከተሉ ተነግሯል። ቤኒን ይህን ድጋፍ እንዲሁም እንደ ጋና፣ ኮትዲቯር እና ሴራሊዮን ካሉ ሌሎች የኢኮዋስ አባላት በይፋ እርዳታ በመጠየቋ ክልላዊ ምላሽ ሊጠናከር ችሏል።
ይህ ሁኔታ በፓሪስ እና ፖርቶ-ኖቮ መካከል ወታደራዊ ግንኙነት እየተጠናከረ በመጣበት ወቅት የተሰማ ነው። የቤኒን ጦር ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ፍሩክቴዩክስ ግባጊዲ፤ ክስተቱ በተፈጠረበት ቀን በፓሪስ የሥራ ጉብኝት ላይ የነበሩ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት የጦር ኃይሎች መካከል ያለው የሥልጠና ልውውጥም እንደቀጠለ ነው ተብሏል። ፓሪስ እና ፖርቶ-ኖቮ ግን ቤኒን ውስጥ ምንም አይነት የፈረንሳይ ጦር ሠፈሮች እንደሌሉ አጥብቀው ይናገራሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ከዚህ ቀደም ፈረንሳይ በናይጄሪያ እና በቤኒን ወታደራዊ ካምፖችን በገንዘብ ደግፋለች በማለት የኒጄር ፕሬዝዳንት ከሰዋል።
የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬም፤ “በእኛ ላይ ያነጣጠሩ ሁለት የፈረንሳይ ካምፖች” ታስተናግዳለች በማለት፤ ቤኒንን ወንጅለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X