- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፡ ለምዕራባዊያን የወገነው ማንነቱ ሲገለጥ

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፡ ለምዕራባዊያን የወገነው ማንነቱ ሲገለጥ
ሰብስክራይብ

''የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ገለልተኛ አይደለም። የፍርድ ቤቱ ፍልስፍናም ያለምንም ማቅማማት የአውሮፓውያን ነው — በተግባር ሲፈተሽ የምዕራቡን የህግ ፍልስፍልና ነው በሥራ ላይ የሚያውለው። የቅኝ ግዛት አሻራ፣ የምጣኔ ሐብት ብዝበዛ ያሉ ስር መሠረቶችን የሚዘነጋ ነው፣ በዚህ የተነሳ ፍትህን ማስፈን ተስኖታል - ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮ አንትሮፖሎጂ መምህሩ መሃመድ አወል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።''

ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከአውሮፓዊ መሠረቱ ባሻገር በዓለም ላይ ለሚፈፀሙ ኢ - ፍትህና እና መድሎዎች መፍትሄ ለመስጠት እንዴት ዓለም አቀፍ ዕይታ የለውም በሚለው ጉዳይ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮ አንትሮፖሎጂ መምህሩ መሃመድ አወል ሀጎስ ሀሳባቸውን ያጋሩናል። አፍሪካ ከውጪ ጣልቃ ገብነት በመላቀቅ አስተማማኝ ልማትን ለማጎልበት ሰላምና ደኅንነትን የሚፈጥር ፖሊሲና ልምምድ ሊኖር እንደሚገባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ኢንቫይሮመንታል መምህሩ ያዛቸው ውድነህ ጋር ያደረግነው ቆይታም የፕሮግራማችን ሌላኛው አካል ነው።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0