የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ምክክር ለማካሄድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠየቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ምክክር ለማካሄድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠየቀ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ምክክር ለማካሄድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠየቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ምክክር ለማካሄድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠየቀ

ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው የምክክር ሂደት ዙሪያ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ “የምክክር ሂደቱ ከትግራይ ክልላዊ ጊዜያዊ አስተዳደር ውጪ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ባካተተ መልኩ በመካሄድ ላይ ነው” ብለዋል።

የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ውይይት ቢደረግም ሕዝቡን ያሳተፈ የምክክር መድረክ ማካሄድ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ 93 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ክፍል መሸፈን ተችሏልም ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0