ኢትስዊች የሀገር ውስጥ የካርድ ሥርዓቶችን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር የብሔራዊ ባንክ ይሁንታን ብቻ እንደሚጠብቅ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትስዊች የሀገር ውስጥ የካርድ ሥርዓቶችን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር የብሔራዊ ባንክ ይሁንታን ብቻ እንደሚጠብቅ አስታወቀ
ኢትስዊች የሀገር ውስጥ የካርድ ሥርዓቶችን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር የብሔራዊ ባንክ ይሁንታን ብቻ እንደሚጠብቅ አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.12.2025
ሰብስክራይብ

ኢትስዊች የሀገር ውስጥ የካርድ ሥርዓቶችን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር የብሔራዊ ባንክ ይሁንታን ብቻ እንደሚጠብቅ አስታወቀ

በዲስከቨር ግሎባል ኔትወርክ አማካኝነት የህንድ ሩፒይ መረብን ጨምሮ ከ32 ዓለም አቀፍ ሥርዓቶች ጋር የሀገር ውስጥ የክፍያ ስርዓትን ማገናኘት የሚያስችል የቴክኒክ ሂደት መጠናቀቁን የኢትስዊች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይልበስ አዲስ ተናግረዋል፡፡

አሠራሩን ተግባራዊ ለማድረግ “ዓለም አቀፍ የክፍያ ማስተናገጃ ሂሳብ” የተሰኘ አዲስ አካዉንት በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ መክፈት ስለሚያስፈልግ ይፋዊ ጥያቄ በማቅረብ ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

"አዲሱ አካውንት፤ በካርድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚደረጉ የድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን በቀጥታ ወደ ውጭ ሀገር በተከፈተ አካውንት መላክ ያስችላል" ሲሉ አስረድተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0