ናይጄሪያ የሲ-130 አውሮፕላን በቡርኪና ፋሶ በድንገት ያረፈው ለጥንቃቂ ሲባል እንደሆነ ገለፀች
17:00 09.12.2025 (የተሻሻለ: 17:04 09.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ የሲ-130 አውሮፕላን በቡርኪና ፋሶ በድንገት ያረፈው ለጥንቃቂ ሲባል እንደሆነ ገለፀች
የናይጄሪያ አየር ኃይል ህዳር 29 ቀን 2018 ወደ ፖርቹጋል በሚያቀናበት ወቅት የሲ-130 አውሮፕላኑ ያጋጠመውን ሁኔታ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።
“ከሌጎስ ከተነሳ በኋላ የበረራ ሠራተኞቹ የቴክኒክ ችግር አስተውለዋል። በዚህም በመደበኛ የደህንነት ሂደቶች እና በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ፕሮቶኮሎች መሠረት በአቅራቢያው በሚገኘው ቦቦ-ዲዩላሶ፣ ቡርኪና ፋሶ ለጥንቃቄ ማረፉ አስፈላጊ ሆኖ ተገኘቷል” ሲል በይፋዊ መግለጫው ጠቁሟል።
“የናይጄሪያ አየር ኃይል ሠራተኞች ደህንነታቸው የተጠበቀ ሲሆን በሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጥሩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል” ሲል የጠቆመው አየር ኃይሉ፤ ተልዕኮው በተያዘለት መርሃ-ግብር መሠረት እንዲቀጥልም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሷል።
የናይጄሪያ አየር ኃይል “በአሠራር ሂደቶች እና በደህንነት መስፈርቶች ላይ ጥብቅ ቁርጠኝነት እንዳለው” በመግለጫው ዳግም አረጋግጧል።
ከዚህ መግለጫ አስቀድሞ የሳኅል ሀገራት ጥምረት ፍቃድ የሌለው ሲ-130 አውሮፕላን የአየር ክልል መጣሱን ተከትሎ “እንዲያርፍ መደረጉን” በመገልጽ ክስ አቅርቧል። በአውሮፕላኑ ውስጥ “ሁሉም ወታደራዊ አባላት ተብለው የተለዩ ሁለት የበረራ ሠራተኞች እና ዘጠኝ ተሳፋሪዎች” መገኘታቸውን አሳውቋል።
ጥምረቱ ክስተቱን በማውገዝ፤ “የሳኅል ሀገራት ጥምረትን የአየር ክልል የሚጥስ ማንኛውም አውሮፕላን ጥቃት ሊፈፀምበት ይችላል” ሲል ያስጠነቀቀ ሲሆን ምርመራም እየተካሄደ መሆኑንም አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X