የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታህሳስ 7 ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተገለፀ
16:00 09.12.2025 (የተሻሻለ: 18:14 09.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ታህሳስ 7 ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተገለፀ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉዟቸው ከኢትዮጵያ አቻቸው ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
የሞዲ ጉብኝት የብሪክስ አባል ሀገራት የሆኑት ኢትዮጵያ እና ህንድ፤ የሁለትዮሽ የልማት ትብብራቸውን የሚያጠናክሩበት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ⓘ ሁለቱ መሪዎች ለመጨረሻ ግዜ በተገናኙበት የደቡብ አፍሪካ የብሪክስ ጉባዔ፤ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ መከላከያ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ግብርና፣ የወጣቶች ክህሎት ልማት እና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ ትብብር ስለማጠናከር ውይይት አድርገው ነበር፡፡
ለመጨረሻ ግዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት የህንድ መሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ ናቸው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X